• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 7 months ago
  • 542 Views

በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገበታ ጨው የሚያመርት ኩባንያ ኢንቨስትመንት

በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገበታ ጨው የሚያመርት ኩባንያ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለፀ

ኤጂ ዋይ የተሰኘ የገበታ ጨው የሚያመርት ኩባንያ በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመግባት የገበታ ጨው ለማምረት ወደ ስራ ይገባል ተብሏል።

ኩባንያው 2000 ካሬ ሜትር የለማ መሬት በመረከብና የራሱን ማቀነባበሪያ በመገንባት ስራ የሚጀምር ሲሆን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታልም ያስመዘገበ ነው።

ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ከ350 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥርም ይሆናል።

አሁን ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለይም በዱቄት ወተት ምርትና ተያያዥ በሆኑ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎች ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶችን እያስተናገደ ሲሆን የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎቻቸውንም እያጠናቀቁ ይገኛሉ።

ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በ2 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን 8 የማምረቻ ሼዶች የተገነቡለት እና ለጅቡቲ ወደብ ቅርበት ያለው ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከል ነው።

A company that produces iodized salt will start operation in Semera Industrial Park

It is said that AGY, a company that produces iodized salt, will enter Samara Industrial Park for production.

The company will begin operation by taking over 2000 square meters of serviced land and building its own processing plant with registered investment capital of more than 250 million birr.

When the company starts operation on a full capacity, it will create job opportunities for more than 350 citizens.

Currently, IPDC is hosting investors who are interested in investing in Semera Industrial Park, especially in powder milk production and related agro-processing sectors, and they are also completing their pre-investment activities.

Semera Industrial Park was built on 2 thousand hectares of land in Semera city of Afar region, and it is a huge investment center which is close to the port of Djibouti with eight production sheds.