• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 7 months ago
  • 543 Views

ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶችና አምራች ኩባንያዎች የተሰጠው ትኩረት

ኮርፖሬሽኑ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶችና አምራች ኩባንያዎች እንዲሁም እንደ ሀገር ትኩረት የሚሹ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እየሰራ እንደሆነ ተገለፀ

ይህንን የገለፁት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከ10 ሀገር በቀል ኩባንያዎች ጋር የውል ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽናቸው እንደሀገር ትኩረት ከተሰጣቸው ከሀገር በቀል ባለሀብቶችና ዋና ዋና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በትልቅ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህም ከእስከዛሬው ለየት ባለ ሁኔታ በዛሬው እለት የውል ስምምነት የተፈራረሙ ኩባንያዎች ሁሉም ሀገር በቀል መሆናቸውና ግማሽ ያህሉ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ አክሊሉ በንግግራቸው ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት የተፈራረሙ ኩባንያዎች በአፋጣኝ ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ አሳስበው ኮርፖሬሽናቸው ለኩባንያዎቹ ያልተቋረጠ የድጋፍና የክትትል ስራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

IPDC is working for local investors and MANUFACTURES as well as investment sectors that need attention as a country.

This was stated by IPDC CEO, Aklilu Tadesse, when he signed a contractual agreements with 10 indigenous companies.

The CEO pointed out that his corporation is working with great focus on local investors and major investment sectors.

He said that it is a great indication that all the companies that have signed contractual agreements today are indigenous and half of them are engaged in the pharmaceutical sector.

Mr. Aklilu, in his speech, urged the companies that have signed a contract with the corporation to enter the production process as soon as possible, and confirmed that the corporation will provide continuous support to the companies.