• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 348 Views

የጀርመን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች

የጀርመን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ኢንቨስት ማድረግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደረገ

በጀርመን ኢኮኖሚና የአየር ንብረት ጥበቃ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስቴር ዩዶ ፊሊፕ የተመራ የልዑካን ቡድን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኝቷል።

ልዑካን ቡድኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬችን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሸን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ኢንቨስተሮች የሚቀርቡ ማበረታቻዎችንና የስራ ዘርፎችን እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለው የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልፀው የጀርመን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

Discussion was held to enable German investors entering and investing in Ethiopian industrial parks

A delegation led by the State Minister, Minister of Economy and Climate Protection Udo Philipp, visited the current activity of the Bole Lemi Industrial Park.

The delegation was welcomed by IPDC CEO, Aklilu Tadesse, and Commissioner of the Investment Commission, Lelise Nemi. They were briefed on the incentives and investment areas offered to investors who invest in Ethiopia, as well as the current activities in industrial parks.

The delegation stated that the current activity in industrial parks is encouraging and that they will do support and monitor German investors to invest in Ethiopia.