• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 368 Views

"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023"

"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023" ኤግዚቢሽን ተጠናቀቀ

"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023" መርሃ ግብር የተለያዩ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቶችን በመፈረም እንዲሁም ፎረሙን በመደገፍ ለተሳተፉ አካላት ዕውቅናን በመስጠት ተጠናቋል ፡፡

በፎረሙ ፕሮግራሞች የፓናል ውይይቶች፣ የኤግዚቢሽን ጉብኝቶችና ምልከታዎች፣ የአንድ ለአንድ ውይይቶች እንዲሁም የስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ ስርአቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለአለም አቀፍ አምራች ኩባንያዎች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም በኤግዚቢሽኑ ለተሳተፉ አካላት ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው የሚገኙ ግብ ተኮር ስራዎች፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሁም ማበረታቻዎችና ምቹ ሁኔታዎችን የሚያሳይ ዝርዝር ማብራሪያ አቅርቧል።

ከኤግዚቢሽኑ መዝጊያ መርሃ ግብር በኋላ የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ ከሚያስተዳድራቸው ፓርኮች መካከል ቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን እንዲጎበኙ የተደረገ ሲሆን በነገው እለት ደግሞ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

"Invest Ethiopia 2023" exhibition has ended.

"Invest Ethiopia 2023" program was completed by signing various MOU agreements and giving recognition to the parties involved in supporting the forum.

Panel discussions, exhibition visits and observations, one-on-one discussions and signing ceremonies of agreement documents have been held in the multi-faceted programs of the forum.

In the program, IPDC as a corporation provided a detailed explanation of the corporation's goal-oriented activities, investment options, incentives, and favorable conditions for international manufacturing companies, investors, and those participating in the exhibition.

After the closing program of the exhibition, the participants of the exhibition were invited to visit Bole Limi & Kilinto Industrial Park, which was built and managed by IPDC, and tomorrow they are expected to visit Dire Dawa Free Trade Zone which is the first Free Trade Zone in Ethiopia.

@Invest_Ethiopia