• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 7 months ago
  • 576 Views

ኮርፖሬሽኑ ያከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች

ኮርፖሬሽኑ ያከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች የባለሀብቶችን የኢንቨስትመንት ፍላጎት ማሳደጉ ተገለፀ

"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችንና ማበረታቻዎችን ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ ያለመ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰትና ለባለሀብቶች የሚደረገውን ድጋፍና ክትትል አስመልክቶ በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

በፓናል ውይይቱ የተገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢንዱስትሪ ፓርኮች በኮሮና ወረርሺኝ እና በሰሜኑ ግጭት አማካኝነት ካጋጠሙት ችግሮች መልሶ በማገገምና ኢንቨስትመንትን በማነቃቃት እንዲሁም የነበሩ የአሰራር ማነቆዎችን በማሻሻል ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል።

ኮርፖሬሽኑ በፓርኮቹ ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የተቀናጀና ቀልጣፋ በማድረግ አሁን በሂደት ላይ ያሉትን ሳይጨምርባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ17 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመው ስራ መጀመራቸውን አቶ አክሊሉ ጨምረው አሳውቀዋል።

ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት የበለጠ ለመጨመርና ያሉትን ማበረታቻዎች ለባለሀብቶች በማስተዋወቅ ላይ ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን ያከሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች ፈጣን አገልግሎት በመስጠት በአፋጣኝ ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023" ኤግዚብሽን በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዘጋጅነት የተለያዩ ተቋማት፣ ድርጅቶች፣ የክልልና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በርካታ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን በማሳተፍ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።