በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የሲሪላንካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የምናከናውነውን የኢንቨስትመንት ሥራ ለማስፋፋት እየሰራን ነው አሉ
በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በጨርቃጨርቅና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ የሲሪላንካ ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ሥራቸውን ለማስፋፋት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
ኩባንያዎቹ ሌሎች የሲሪላንካ ባለኃብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የማስተዋወቅ ሥራ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ኢንዶቺን የተሰኘው የልብስ አምራች ፋብሪካ የቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ አኖጅ ራናዌራ ኩባንያው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሥራውን ለማስፋት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።
ከሰባት ዓመታት በፊት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራውን የጀመረው ኩባንያው አሁን ላይ ከ5000 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የሥራ እድል መፍጠሩን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጨርቃጨርቅ ምርት ላይ የተሰማራውና ከ10 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር የቻለው ጄጄ የተሰኘው ኩባንያ አስተዳዳሪ ዲላን ማዳሻንኩ ኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ ያላት አገር መሆኗን ተናግረዋል።
የኩባንያዎቹ ተወካዮች ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት ሀብት ከግምት በማስገባት የሲሪላንካ ባለኃብቶች በግብርናና በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ እያደረግን ነው ብለዋል።
@Ethiopian_news_agency