የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ
የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የተወያዩ ሲሆን ገንቢና አስቻይ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
በውይይቱም ባለፉት 4 አመታት እንደሀገር የተመዘገቡ ለውጦችና ድሎችን በቋሚነት ለማፅናትና በየግዜው የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን አስቀድሞ በፅናት እና በብቃት የመሻገር አቅም መፍጠር የሚቻልባቸው ነጥቦች ትኩረት ተደርጎባቸዋል።
በመጨረሻም ኮርፖሬሽኑ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ያሉ ኢንቨስተሮችን ውጤታማ እንዲሆኑ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ ተጨማሪ አለማቀፍና ሀገር በቀል ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ የውጪ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግና ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠርና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ በሙሉ ትኩረት የሚሰሩ ዋነኛ ተግባራት መሆናቸዉ ተገልጿል።