• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 5 months ago
  • 384 Views

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የአለም ባንክ ድጋፍ

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚገነባ ግዙፍ የክትባት ማምረቻ ፋብሪካ የአለም ባንክ 30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የክትባት ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችል 30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለዚሁ አላማ የሚገነባው የክትባት ፋብሪካ የግል ዘርፉን ባለሀብቶች የሚያሳትፍ መሆኑንም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ በመድኃኒት አምራች ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ከሚፈልጉ 20 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ጤና ሚኒስቴር የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመ ሲሆን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፋብሪካውን የገነባው 'አፍሪኪዩር ፋርማሲቲካልስ' እና በደብረብርሀን ኩባንያውን የተከለው 'ትረስት ፋርማሲዩቲካል' የተሰኙ አምራች ኩባንያዎች በቅርብ ወራት ወደ ምርት ሂደት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ጋር ክትባቶቹን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በቅርቡ በዝርዝር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።

@Ethiopian_Broadcasting_Corporation