በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ የተመራ ልዑክ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የስራ ጉብኝት እያካሄደ ነው
ነፃ ንግድ ቀጠናን ከማልማት፣ ከማስተዳደር እና ከተያያዥ ጉዳዮች ጋር ውጤታማ ስራ ለመስራት ያለመ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እየተካሄደ ይገኛል
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የተመራ ልዑክ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
ልዑኩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዲፒ ወርልድ በተሰኘ ተቋም ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የተቋሙን የመካከለኛ ምስራቅ እና አፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱሀኢል አልባና ጋር ተገናኝቶ በዝርዝር ተወያይቷል።
በውይይቱም የነፃ ንግድ ቀጠና ልማት፣ አስተዳደርና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ገንቢ ሀሳቦች ተነስተው ከመግባባት ተደርሷል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ነፃ ንግድ ቀጠናዎችን ለማቋቋም አለም አቀፍ ልምድ እና አሰራሮችን ለመቅሰም በተለያዩ ሀገራት ይፋዊ ጉብኝት እና ግንኙነቶችን እየፈጠረ ይገኛል።
An official visit is being conducted with the objective of developing and managing Free Trade Zone and other related issues.
A delegation led by IPDC CEO, Aklilu Tadesse, is on an official visit in the United Arab Emirates.
The delegation visited the headquarters of DP World in the United Arab Emirates and met with Suhail Albanna, CEO and Managing Director Middle East and Africa in DP World, and had a detailed discussion.
In the discussion, mutual agreement was reached on constructive ideas to work together on the development and management of Free Trade Zone and other related issues.
IPDC is making official visits and contacts in various countries to gain international experience and practices to make Dire Dawa Free Trade Zone effective and to establish other free trade zones.