• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 8 months ago
  • 795 Views

ክትባቶችን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማምረት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ክትባቶችን ለማምረት መሰራት በሚገባቸው  የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለክትባቶች ግዢ የምታወጣውን ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ለማዳን ምርቶቹም በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በማምረት ለመተካት እንዲቻል ስራ ለመጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወደ ተግባር ለመግባት በሚቻልባው ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ 

በ279 ሄክታር መሬት ላይ የተሰራው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በህክምና ግብዓቶችና መድሃኒቶችን በማምረት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የተዘጋጀ የፋርማሲዩቲካል ፓርክ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ከ14 በላይ ባለሃብቶች በዘርፉ ተሰማርተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ 

A discussion was held on possible issues for the production of vaccines, which cost more than 100 million $ annually. 

Aklilu Tadese, CEO of Industrial Parks Development Corporation, discussed with H.E Dr. Liya Tadese, FDRE Minister of Health, the common issues that should be done to produce vaccines in Kilinto Industrial Park. 

A consensus has been reached In order to save the cost of more than 100 million dollars that Ethiopia spends on the purchase of vaccines every year, to produce and replace the vaccines in Klinton Industrial Park. 

Kilinto Industrial Park, built on 279 hectares of land, is dedicated for pharmaceutical sector for investors who are engaged in the production of medical supplies and medicines, and currently more than 14 investors are working in the sector.