ተቀማጭነታቸውን ቤላሩስ ያደረጉ ለማዕድን ማውጣት አገልግሎት የሚውሉ መኪኖችን እና የሞተር ክፍሎችን እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለማምረት ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን ተወካዮች በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስትመንታቸው እውን መሆን ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ኮርፖሬሽኑ የሚያቀርባቸውን ኢንቨስትመንት ተኮር አገልግሎቶች፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ገንብቶ የሚያስተዳድራቸውን ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ምቹ ሁኔታዎችን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ለኩባንያዎቹ የቀረቡ ሲሆን ኩባንያዎቹም ስለኢንቨስትመንታቸውና መስራት ስለሚያስቡት ስራ ዝርዝር መረጃዎችን አቅርበዋል።
ኩባንያዎቹ በቀጣይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ለማምረት የሚያስችላቸውን የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎች እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።
Belarus - based companies that manufacture cars and engine parts for mining, as well as medical equipment, have expressed interest in manufacturing in industrial parks.
IPDC CEO, Aklilu Tadesse, received the representatives of the companies in his office and assured that the corporation will provide continuous support to make their investment a realty.
Detailed information regarding the investment-oriented services provided IPDC, the State of The Art industrial parks it has built, as well as investment incentives and favorable conditions have been provided to the companies. The companies have also provided detailed information about their investments and the work they intend to do.
It is stated that the companies will continue to carry out pre-investment activities that will enable them to start Production in industrial parks.