• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 2 months ago
  • 371 Views

የኢንዱስትሪ ፓርኮች የኢንቨስትመንት ተመራጭነት

በ2030 ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን ለማስቻል መንግስት በርካታ የሀገር በቀል ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡

በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል፤ ከፍተኛ የስራ እድል ፈጠራ እና የክህሎት ሽግግር እንዲኖር የቴሌኮም፣ኢነርጂና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፉን ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ወደ ግል የማዞር ስራ በኢትዮጵያ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በመጨመር ለዘርፉ እድገት ትልቅ አስተዋጾ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ቢያደርጉ የሚኖሯቸው ጠቀሜታ ከሌሎች ሃገራት አንጻር ምን የተለየ ያደርገዋል?

የኢትዮጵያ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት 46 በመቶ እድገት ያለው ሲሆን ይህም በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ተቀባይ ሀገር ያደርጋታል፡፡

ኢትዮጵያ በአለም ገበያ ላይ እጅጉን ተፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን እንደ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ቡና፣ ሻይና ሌሎች ቅመማ ቅመሞችን ለማምረት ምቹ የአየር ጸባይና ለም አፈር ያለው መሬት አላት፡፡

ኢትዮጵያ ባላት ለም አፈር መሬት ምክንያት ቡናን በማምረት በአለም ቀዳሚ እና በኮፊ አረቢካ ዘር በአለማችን ሶስተኛዋ አምራች ሀገር ስትሆን አበባን ወደ አውሮፓ ህብረት ገበያ በመላክ ቀዳሚዋ እንዲሁም ከአፍሪካ ትልቋ ሁለተኛ የአበባ ላኪ ሀገር ናት፡፡

ኢትዮጵያ በህዝብ ብዛቷ ከአህጉሪቱ ሁለተኛ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከ70 በመቶ በላይ ደግሞ ከፍተኛ የመስራት አቅም ያለው ወጣት ሀይል ያላት እና ወደ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎችን የያዙ ከ50 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከ380 ሺ በላይ ተማሪዎችን እያስተማሩ ያሉ ከ1500 በላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ይገኛሉ፡፡

ይምጡ በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ በተገነቡት ኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን
በመረጡት ዘርፍ ኢንቨስት አድርገው ትርፋማ ይሁኑ!

በኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን ፀሃይ አትጠልቅም!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን!