በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና የፋይናንስ ተቋማትን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ ዳሸን ባንክ እና እናት ባንክ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ገብተው ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
የፋይናንስ ተቋማቱ በነፃ የንግድ ቀጠናው የሚሰጠውን የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ በማሳለጥ በኩል የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡና ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶችም ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ በስምምነቱ ወቅት ገልፀዋል።
Progressive works are being done to increase the participation of financial institutions in Dire Dawa Free Trade Zone.
Industrial Parks Development Corporation has signed a memorandum of understanding with 4 banks that provide financial services in Dire Dawa Free Trade Zone.
Commercial Bank of Ethiopia, Cooperative Bank of Oromia, Dashen Bank and Enat Bank have signed an agreement allowing them to enter and operate in Dire Dawa Free Trade Zone.
Aklilu Tadesse, IPDC CEO, stated during the agreement that the financial institutions will play a great role by providing facilitated financial services for the free trade zone and will be able to provide convenient and efficient services to investors.