• Striving for eco industrial park
logo

የእንግሊዝ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ የልዑካን ቡድን የቂሊንጦ እና የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኙ

የእንግሊዝ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ የልዑካን ቡድን የቂሊንጦ እና የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኙ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው የተለያዩ የእንግሊዝ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ልዑካን የቂሊንጦ እና የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን የጎበኙ ሲሆን፤ በቆይታቸውም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በኢንቨስትመንት ሁኔታዎች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ልዑካን ቡድኑ በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በነበረው ጉብኝት ከኮርፖሬሽኑ የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ጃለኔ ሃሰን እና የኦፐሬሽንና ፓርክ አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ከተማ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

በውይይቱ ወቅት የኦፐሬሽንና ፓርክ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ከተማ ኮርፖሬሽኑ ስለሚያስተዳድራቸው 14 የኢንቨስትመንት ማዕከላት እና በውስጣቸው ስላሉ ከ250 በላይ ባለሀብቶች የሥራ እንቅስቃሴ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። አቶ ፍጹም አክለውም፣ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ መዋለ ንዋያቸውን ፈሰስ ለሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ስለሚሰጡ ማበረታቻዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ ኩባንያዎቹ ወደ ሥራ በሚገቡበት ወቅት ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የልዑካን ቡድኑ በሁለቱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ባደረገው የመስክ ምልከታ፤ በዞኖቹ ውስጥ የተገነቡትን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶችና ለባለሀብቶች የተዘጋጁ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በዝርዝር ተመልክተዋል። በተለይም በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በፋርማሲዩቲካል የኢንቨስትመንት ዘርፍ ቢሰማሩ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ጸጋ እና መንግሥት ለዘርፉ ስለሚሰጣቸው ልዩ ድጋፎች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የእንግሊዝ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ልዑካን ተወካዮች በበኩላቸው በሁለቱ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ባደረጉት ጉብኝትና በተደረገላቸው ገለጻ መደሰታቸውን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚሰሩ አመልክተዋል።

UK Delegation Explores Investment Opportunities in Ethiopia’s Industrial Parks

A UK business delegation has visited Ethiopia to examine potential investment prospects and evaluate the country’s industrial park infrastructure overseen by the state-owned Industrial Parks Development Corporation (IPDC).

The group, made up of representatives from various British companies, toured the Kilinto and Bole Lemi Special Economic Zones (SEZs). The visit was designed to give the delegation a clearer understanding of Ethiopia’s industrial capacity and to identify possible areas for partnership and investment.

At Kilinto SEZ, the delegation met with senior officials, including Chief of Staff Jalene Hassen and IPDC’s Chief of Operations and Park Management, Fitsum Ketema.

During a briefing, Fitsum Ketema noted that IPDC currently manages 14 key industrial hubs, which host over 250 active investors. He also highlighted the range of incentives available to foreign investors and underscored the government’s efforts to maintain a favorable business environment.

According to him, IPDC provides end-to-end administrative and professional support to help investors move efficiently from project initiation to full-scale operations.

The delegation’s visits to Kilinto and Bole Lemi SEZs offered practical exposure to the parks’ infrastructure and specialized industrial clusters, helping them better assess Ethiopia’s investment landscape.