• Striving for eco industrial park
logo

አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን ጎበኙ

አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ሀገሪቱ ክፍል ገንብቶ የሚያስተዳድራቸው የኢንቨሰትመንት ማእከላት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ ከማመላከት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት የዚህ ታሪካዊ ሂደት አካል እንዲሆኑ ለማስቻል ታልሞ የተዘጋጀ ነው፡፡

ከሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ጉብኝት በተጨማሪ ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉበትን የስራ እንቅስቃሴ ለመገንዘብ የሚያስችል ገለጻ የተደረገላቸው አምባሳደር ፍጹም የቶዩ ሶላርን የስራ እንቅስቃሴንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ ኮርፖሬሽኑ አልሚ ባለሀብቶችን ከሁሉም የዓለም ክፍል ለመሳብ የሚያደርገውን ጥረት ያግዛል ተብሎ ይታመናል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የዲያስፖራ ማህበረሰቧ ጋር የሚያገናኝ ተቋማዊ መድረክ ሲሆን በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ልማት ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታት ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ትስስሮች ማጠናከርን ዋና ተልዕኮው አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል።

ተቋሙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት ከሀገራቸው ጋር በተጠናከረ መልኩ በማስተሳሳር የተባበረች፣ የተረጋጋች እና የበለፀገች ኢትዮጵያ ለመገንባት የጋራ ራዕይን እና ኃላፊነትን ያጎልብታል ተብሎ ይታመናል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተቀናጀ መሰረተ ልማትን በአንድ ቦታ ለባለሃብቶች በማቅረብ ባለሃብቶች ምንም የቢሮክራሲ ውጣ ውረድ ሳይገጥማቸው ባጠረ ጊዜ ወደ ስራ እንዲገቡ በማስቻል ሃገራዊ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማፋጠን የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡