የኢትዮጵያ ኢንቪስትመት ሆልዲንግ አመራሮች የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠናን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
በኢትዮጵያ ኢንቪስትመት ሆልዲንግ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል የተመራ የአመራሮች ቡድን የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠናን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
የኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የድሬ ዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠናን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ያደረገውን ጥረት ያደነቀው የአመራር ቡድኑ ነጻ ንግድ ቀጠናው ወደ ስራ ከገባ ወዲህ እያስመዘገባቸው ያሉት ውጤቶች አበረታች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ነጻ ንግድ ቀጠናው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ መግባቱን የተመለከቱት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አመራሮች ቀጠናው ለሀገር ኢኮኖሚ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት እንዲቻል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል፡፡
የነጻ ንግድ ቀጠናው አሰራር በመስረታዊነት ሊቀይሩ የሚችሉ ባለሀብቶችን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን ለመሳብ በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡
የድረዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ከገባ አንድ አመት ገደማ የሆነው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ በንግድ፣ በሎጀስቲክ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ከ50 ባለሀብቶችን በመሳብ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡
የኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የድረዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠናን ጨምሮ 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን እና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በስሩ የሚያስተዳድር ትልቅ ሀገራዊ ተቋም ሲሆን ኢንቪስትመት ሆልዲንግ ስር ከሚተዳደሩ ከ40 በላይ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30