• Striving for eco industrial park
logo
  • by ipdcadmin
  • 0Comments
  • 10 hours, 44 minutes ago
  • 25 Views

ኢትዮጵያ ከልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቿ ከሚላኩ ምርቶች ከአንድ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሚቀጥለው ዓመት ታገኛለች- ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ከልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቿ ከሚላኩ ምርቶች ከአንድ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሚቀጥለው ዓመት ታገኛለች- ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)


ኢትዮጵያ ከልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ለውጪ ሀገር ገበያ ከሚቀርብ የኢንዱስትሪ ምርት አንድ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህንን የገለጹት ከሩሲያው የዜና አገልግሎት ስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ከሰሞኑ በነበራቸው ቆይታ ነው፡፡ ዶ/ር ፍሰሃ የኮርፖሬሽኑ የስድስት ወር የኤክስፖርት አፈጻጸም ከ112 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ መሆኑን ጠቁመው ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ማደጉን አብራርተዋል፡፡ በበጀት አመቱ ማጠቃለያ ላይ በኮርፖሬሽኑ ከሚተዳደሩ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ባሉ አምራቾች ተመርተው ወደ ውጪ ከሚላኩ ምርቶች የሚገኘው የውጪ ምንዛሬ 300 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይሻገራል ብለው እንደሚጠብቁ አመላክተዋል፡፡

ለውጪ ምንዛሬ ግኝቱ ማደግ ኮርፖሬሽኑ የተገበራቸው የማሻሻያ ስራዎች ከሀገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎች ጋር ተናበው መተግበራቸውን ጠቁመው ኮርፖሬሽኑ የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱን ተግባራዊ ማድረጉን እንደ ማሳያ አንስተዋል፡፡
እስትረቴጂክ እቅዱ በዋነኛነት ዘርፍ ብዙ የኢንቨሰትመንት ስበትን ማዕከል እንዳደረገ አብራረተዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ወደሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የሚገቡ ኩባኒያዎች የሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ እና የኢንቨትመንት ምንጭ የሆኑ ሀገራትን ለማስፋት ታቅዶ ሲሰራ መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡

ኮርፖሬሽ በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ከዚህ ቀደም ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ላይ ያተኩሩ የነበሩት ቀላል ኢንዱትሪዎች ዛሬ ላይ ወደ ሀይቴክ እየተለወጡ እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ ይህም ሀገሪቱ ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች የሚገኘውን የውጪ ምንዛሬ በሚቀጥለው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እንዲሻገር ያስችላል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ፍሰሃ በሀገሪቱ በተገነቡት 14 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሬ ግኝቱን ከማሳደግ ጎን ጎን የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚጫወተውን ሚና ማሳደግ ላይም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸውን የኢኮኖሚ ማዕከላት እንደ ዋነኛ የልማት ምሰሶ በመጠቀም ኢትዮጵያ በገቢ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነትን ለመቀነስ እና የሎጂስቲክስ አማራጮቿን ለማስፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አመላክተዋል፡፡በዚህ ረገድ የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና የሚጫወተውን ሚና ያብራሩት ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በጅቡቲ ወደብ ላይ ያለውን ከፍተኛ መጨናነቅ ለመቀነስና የንግድ ፍሰቱ ፈጣን፣ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳ አብራርተዋል፡፡

ሀገሪቱ ከውጩ ወደደ ሀገር ውሰጥ የምታስገባቸው ምርቶች እና ወደ ውጪ የምትልካቸውን ምርቶች ሂደት በማፋጠን በሚቀጥሉት አምስት አመታት ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ንግድን የማሳለጥ (Trade Facilitation) ስራ በነጻ ንግድ ቀጠናው ይስራል ተብሎ መታቀዱን የኮርፖሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ከሚዲያ ተቋሙ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የድርድር አቅም እንደሚያሳድጉላት እና የራሱን ምርት የሚያመርት አገር ሙሉ ሉዓላዊነት ሊኖረው አይችልም ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በBRICS አባል አገራትና በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት ሰፊ ገበያ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል ከውጭ ይገቡ የነበሩ የጸጥታ ተቋማት ዩኒፎርም፣ ቢራ ለመጥመቅ የሚያገለግል ብቅል እና የመድኃኒት ምርቶች አሁን በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ እንዲመረቱ በመደረጉ ከዚህ ቀደም ከውጪ ይገባ የነበረ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካቱን እንደማሳያ አንስተዋል።

ከዚህ በፊት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የውጭ ባለሀብቶች ድርሻ 90 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በተሰራ  የማሻሻያ ስራ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ድርሻ ወደ 60 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉን የገለጹት ዶ/ር ፍሰሃ ፣ ኢንዱስትሪው በሀገር በቀል አቅም ላይ እንዲመሠረትና ለበርካታ ዜጎች ጥራት ያለው የሥራ ዕድል እንዲፈጥር ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከሚዲያው ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል፡፡

#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
#sputnikafrica

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30