• Striving for eco industrial park
logo

ባለፉት 6 ወራት ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

ባለፉት 6 ወራት ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች ከ13.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

የኮርፖሬሽኑ የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደተገለጸው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ ከ13 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምርት ኮርፖሬሽኑ በሚስተዳደድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሀብቶች ለገበያ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ለገቢው ማደግ የሃገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር በመንግስት በኩል የተደረጉ የማሻሻያ ስራዎች መሆናቸውን የተገለጸ ሲሆን ባለፉት 6 ወራት ለሀገር ውስጥ ገበያ የቀረበው የምርት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ61 በመቶ ዕድገት ማሳየት መቻሉ ተጠቁሟል።

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች በሚገኙ ኩባንያዎች በጀት ዓመቱ ለሃገር ውስጥ ገበያ የቀረበው ምርት ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ተጠቁሟል፡፡ የምርት አቅርቦቱ ቀጣይነት እንዲኖረው በትኩረት እንደሚሰራም ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ74 ድርጅቶች ከ4800 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ዘላቂ የሆነ ተጨማሪ የገበያ ትስስር መፍጥር የቻሉ ሲሆን በተፈጠረው የገበያ ትስስር ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸም መቻሉ ተገልጿል፡፡


#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#solarpanels
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30