• Striving for eco industrial park
logo

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 6 ወራት ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 6 ወራት 2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል።

 

ኮርፖሬሽኑ በአዳማ ከተማ ባካሄደው የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደተገለጸው፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ውስጥ 2.87 ቢሊዮን  ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ፣ በተግባር 2.7 ቢሊዮን  ብር ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን ይህም የእቅዱን 93.6 በመቶ ማሳካቱን ተችሏል ተብሏል።

 

የኮርፖሬሽኑ የገቢ አሰባሰብ አቅም በየዓመቱ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ የመጣ መሆኑ ተመላክቷል:

 

ኮርፖሬሽኑ 2018 በጀት ዓመት ግማሽ ላይ ብቻ የሰበሰበው ገቢ ከ2017 በጀት ዓመት ጠቅላላ ገቢ ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ እድገት እያመጣ እንደሆነ ያመለክታል:: ለገቢው መጨመር ኮርፖሬሽኑ ሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና  ኢንዱስትሪ ፓርኮች የየአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን የገቢ ምንጮችን ለማስፋት የተሰሩ የማሻሻያ ሥራዎች ውጤት እያስገኙ መምጣታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

 

 

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ወደ ሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች 377 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስመዘገቡ 64 ባለሃብቶችን  መሳቡ ይታወሳል፡፡

 

በተመሳሳይ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው በመስራት ላይ በሚገኙ ባለሃብቶች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 112.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ይታወሳል፡፡