• Striving for eco industrial park
logo

የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ፓርክ ኮርፖሬሽን አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ የመጀመሪያ ሰብሰባውን አደረገ

የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ፓርክ ኮርፖሬሽን አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ የመጀመሪያ ሰብሰባውን አደረገ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተቀጽላ ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ኮርፖሬሽን አዲሱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የመጀመሪያ ስብሰባቸውን አደረጉ።

የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ኮርፖሬሽን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ወደ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መተላለፉን ተከትሎ ለኮርፖሬሽኑ አዲስ የቦርድ አባላት ተሰይሞለታል፡፡

የቦርድ አባላቱም ዛሬ የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ያካሄዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ኮርፖሬሽን እያጋጠሙት ያሉ ችግሮችን በአጭርና በረጅም ጊዜ ሊፈታ የሚችልበትን አግባብ በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ፓርክ ኮርፖሬሽን የስራ አመራር ቦርድ አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወርቁ ጋቸና ሰብሳቢ፣ ሲሆኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ ይታገሱ፣ የኢትዮጵያ ኑክለር ኢነርጅ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሳንዶካን ደበበ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ይድነቃቸው ወርቁ ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ፤የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመው፣የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዝናቡ ይርጋ ደግሞ በአባልነት ተሰይመዋል።


የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ወደ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ከመተላለፉ በፊት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና ዳታ ማይኒንግ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የተቋቋመ መሆኑ ይታወሳል፡፡

#IPDC
#PMOEthiopia
#ecospecialeconomiczone
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#bolelemiSEZ
#kilintoSEZ
#addisindustryvillage
#informationtechnologypark
#AdamaSEZ
#jimmaSEZ
#HawassaSEZ
#debrebirhanSEZ
#bahirdarSEZ
#kombolchaSEZ
#Arertiindustrypark
#MekeleSEZ
#DDFTZ
#semeraSEZ
#textilehub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#fdiready
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#pharmahubafrica
#eastafricasez
#GoldenOpportunity
#itparks
#information
#informationtechnology
#InnovationLeadership
#InnovationInAction
#SolarPanels
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30

Information Technology Park Corporation - Ethiopia