• Striving for eco industrial park
logo

የሃገር ውስጥ አምራቾችን የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በበመፍታት የሃገርን ኢኮኖሚ እንዲደግፉ ለማድረግ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ወሳኝ

የሃገር ውስጥ አምራቾችን የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በበመፍታት የሃገርን ኢኮኖሚ እንዲደግፉ ለማድረግ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ወሳኝ ነው:-ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

 

አምራች ኢንዲስትሪያሊስቶች በሁለንተናዊ ዘርፉ የሚያጋጥማቸውን ተግዳሮቾች በመፍታት የሃገር ኢኮኖሚን ከመደገፍ ባለፈ ሃገራችንን የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ።

 

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት የሃገር ውስጥ አምራቾችን በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው እንዲሰሩና ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የሃገር ኢኮኖሚን ለመደገፍ ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በተፈራረሙበት ወቅት ነው።

 

የመግባቢያ ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ተፈራርመዋል።

 

ዶ/ር ፍሰሃ በስምምነቱ በሃገር ውስጥ የሚገኙ አምራቾችን በመሰረተ ልማት፣በመስሪያ ቦታ፣በገበያ ትሥሥር እንዲሁም በግብዓት ትስስር በመፍጠር በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ኮርፖሬሽኑ በሁሉም ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን ገልጸዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱ የሃገር ውስጥ አምራርቾን ለማበረታታት እና ውጤታማ ለማድረግ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመስራት ለሃገር ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ የሚያደርግ ባለሃብት ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል ።

 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሃገር ውስጥ አምራቾችን ለማበርታታት ልዩ የእፎይታ ጊዜን ጨምሮ የኪራይ ቅናሽ እንዲሁም የድጋፍና ክትትል ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን በዛሬም ስምምነትም አምራቾችን የማሰልጠንና የማማከር፣የማምረቻ ቦታ የማቅረብ፣የገብያ ትስስር መፍጠር፣ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ እንዲልኩ የመደገፍ እንዲሁም የተሞክሮ ቅመራና የልምድ ልውውጥ ስራዎች በሁለቱ ተቋማት በኩል የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።

 

 

#IPDC #PMOEthiopia #striving_for_eco_industrial_park #industrialpark #ecoindustrialpark #Investment #ForeignDirectInvestment #Importsubstitution #exportprocessingzone #SpecialEconomicZones #madeinethiopia #madein #exportprocessingzone #SpecialEconomicZones #madeinethiopia #madein #InvestInEthiopia #InvestEthiopia #HawassaSEZ #TextileHub #PlugAndPlay #AfricaRising #manufactureinafrica #GoldenOpportunity #TechManufacturing #InvestEthiopia #FDIReady #StrategicInvestments #TechManufacturing #PharmaHubAfrica #FDIReady #EastAfricaSEZ #GoldenOpportunity #HawassaSEZ #InvestEthiopia #itparks #information #informationtechnology #innovation #InnovationInAction #ethiotelecom #zemengebya በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30