• Striving for eco industrial park
logo

የማይቋረጥ የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ልማት የልብ ትርታ ነው - ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

የማይቋረጥ የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ልማት የልብ ትርታ ነው - ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)


የማይቋረጥ የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ ልማትና ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን የገለጹት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመተባበር በታላቁ የህዳሴ ግድብ መገኛ ጉባ ላይ ባዘጋጀው "ስለ ኢትዮጵያ" መድረክ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ ነው።

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኃይል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ያደረገችው ኢንቨስትመንት ለዛሬው ኢኮኖሚያዊ ለውጥ መሠረት መሆኑን ዶ/ር ፍሰሃ ጠቅሰዋል።

ሀገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አሁን ያላትን የኃይል አቅርቦት ቢያንስ በአስር እጥፍ ማሳደግ እንደሚገባት አሳስበዋል።

ለዚህም እንደ አብነት ግብፅን የጠቀሱ ሲሆን፣ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት 60,000 ሜጋ ዋት አካባቢ ኃይል ለዜጎቿ እያቀረበች መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እየመጡ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አመልክተዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ፓርኮች 2,500 ሜጋ ዋት አካባቢ ኃይል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ለአብነትም አንድ የአሉሚኒየም ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት ያሳየ ኩባንያ ብቻውን ከአንድ ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ኃይል እንደሚፈልግ እንደ ማሳያ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ማዕከል ሆና እንድትወጣና ዓለም አቀፍ ካፒታልን ለመሳብ የኃይል አቅርቦት ዋነኛ መወዳደሪያ መሆኑን ዶ/ር ፍሰሃ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም የታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ለኢንዱስትሪ መስፋፋት፣ ለቱሪዝም እድገት፣ ለክልላዊ ትስስርና ብሔራዊ አንድነትን ለሚያጠናክሩ አሰባሳቢ ትርክቶች ያለውን ፋይዳ በተመለከተ በፓናል ውይይቱ ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

 
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone 
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein 
#exportprocessingzone 
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia 
#HawassaSEZ 
#TextileHub 
#PlugAndPlay 
#AfricaRising 
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady 
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#HawassaSEZ 
#InvestEthiopia
#itparks 
#information 
#informationtechnology 
#innovation 
#InnovationInAction
#ethiotelecom
#Zemengebya

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30