በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በዲጅታል አማራጭ ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና ኢትዮ ቴሌኮም በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በ'ዘመን ገበያ' ለሀገር ውስጥ ገበያተኞች ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል::
የስምምነት ፊርማውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተፈራርመዋል::
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾች ምርቶቻቸውን ወደ ዘመን ገበያ በማስገባት፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳጅና ትልቅ ስም ያላቸው ምርቶችን፣ ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ለማቅረብ ከማስቻሉ በተጨማሪ ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሃገራችን አንጋፋ ከሆነው ሃገራዊ ተቋም ኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ፍስሃ በተጨማሪም ስምምነቱ በዲጂታል ግብይት ዘርፍ የዲጂታል 2030 ስትራቴጂን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝና በጅምር ላይ የሚገኘውን የሃገራችን የኤሌክትሮኒክ የግብይት ስርዓት በመደበኛነት ለማስቀጠል ትልቅ ዕድል መፍጠር ያስችላል ብለዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው የሀገራችን የግብይት ሥርዓት በዲጂታል በማዘመን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል፣ ሁሉን አቀፍ እና አካታች የሆነውን 'ዘመን ገበያ' የተሰኘ ዘመናዊ የዲጂታል ግብይት ፕላትፎርም ማስጀመሩን ገልጸው በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ አምራቾችም ፕላትፎርሙን ተጠቅመው ምርቶቻቸውን በሰፊው የማስተዋወቅና አስተማማኝ የገበያ ትስስር በመፍጠር አጠቃላይ የሀገራችንን የንግድ ሥነ ምህዳር ወደ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነው ብለዋል::
ስምምነቱ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ አምራቾች የኤክስፖርት ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶቻቸውን በስፋትና በተቀላጠፈ ሁኔታ ተደራሽ እንዲያደርጉ ያግዛል ተብሏል::
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሃገሪቱ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው 11 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና 3 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከ 200 በላይ ትልልቅ ስምና ዝና ያላቸው አምራቾች ያሉ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የተቀናጀና የቴሌኮም እና የዲጂታል መፍትሄዎች አቅራቢ ኩባንያ ነው::
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#GoldenOpportunity
#TechManufacturing
#InvestEthiopia
#FDIReady
#StrategicInvestments
#TechManufacturing
#PharmaHubAfrica
#FDIReady
#EastAfricaSEZ
#GoldenOpportunity
#HawassaSEZ
#InvestEthiopia
#itparks
#information
#informationtechnology
#innovation
#InnovationInAction
#ethiotelecom
#Zemengebya
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30