የቻይና የባለሃብቶች ልዑካን ቡድን የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን ጎበኘ
ሀያ ስድስት አባላትን ያቀፈ የቻይና ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላትን ተቀብለው ያነጋገሩት የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ ተወካይ አቶ ታሪኩ አዱኛ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶችና ለባለሃብቶች በሚሰጡ የተለያዩ ማበረታቻዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው በፋርማሲዩቲካል የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለባለሃብቶች በሚሰጡ ማበረታቻዎችና በመንግስት በኩል የሚደረገውን ድጋፍ አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ የሚሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የፋርማሲዩቲካል የኢንቨስትመንት ዘርፍን ለማበረታታት በመንግስት በኩል የሚደረጉ ድጋፎችንና በኮርፖሬሽኑ በኩል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ምስክር ማሞ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 11 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና 3 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው በመስራት ላይ ካሉ የውጪ ባለሃብቶች ውስጥ ቻይናውያን ባለሃብቶች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡
#IPDC
#EcoGreenSEZs
#GreenIndustrialization
#CircularEconomy
#GreenLegacyInitiative
#EVTransport
#SustainableManufavcturing
#ClimateResilience
#LowCarbonDevelopment
#Ethiopia
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#pharmaceuticals
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30