ኮርፖሬሽኑ ዓለም ዓቀፍ ደረጃን ያሟላ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የተቀናጀ የስራ አመራር ስርዓት ለመተግበር ስልጠናዎች እየሰጠ ነው
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዓለም ዓቀፍ ደረጃን ያሟላ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የተቀናጀ የስራ አመራር ስርዓት ለመተግበር የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ለአመራሩ እና ለሰራተኛው በመስጠት ላይ ነው፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከዋና መስሪያ ቤት በተጨማሪ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ደረጃውን የጠበቀና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት በዞኖቹ ውሰጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በጥራት ስራ አመራር ስርዓት ዘርፍ፤ በስራ ላይ ደህንነት ስራ አመራር ዘርፍ እና በአካባቢ ጥበቃ ስራ አመራር ዘርፍ እውቅና ለማግኘት የሚያስችል ስራዎችን የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከዋና መስሪያ ቤትና ከልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ለተውጣጡ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡
በተከታታይ ዙሮች በተሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሶስቱን ዘርፎች በማቀናጀት እውቅና ለማግኘት የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት ሁሉም ባለሙያና አመራር ግንዛቤ ወስዶ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን በስልጠናው መክፈቻዎች ላይ ተገልጿል፡፡
ስልጠናውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#pharmaceuticals
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30