የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ስራ እዲጀምሩ ጥሪ ቀረበ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ስራ እዲጀምሩ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከተገኙ የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባኒያ ባለቤቶች ጋር በነበራቸው ውይይት ባለሀብቶቹ በድሬ ዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ሀብታቸውን እና እውቀታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ከወሰኑ ኮርፖሬሽኑ ደረጃውን የተጠበቀ መሰረተ ልማት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚያቀርብላቸው ገልጸዋል፡፡
በፎረሙ ኢትዮጵያ በትራንስፖርት፣ በሎጀሰቲክ እና መሰረተ-ልማት ዘርፍ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ከማብራራታቸው በተጨማሪ በኢትዮጵያ እያደጉ የመጡ ሀገራዊ እስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንቶችን እድገት ለመደገፍ የሚያስፈልጉ የትራንስፖርት እና የሎጀሰቲክ ዘርፍ ለውጪ ቀጥተኛ አንንቨስትመንት ክፍት መደረጋቸውን አብራርተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን እንደ ተቋቋመ አንድ የመንግስት ልማት ድርጅት የውጪ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን ስራ ላይ ሲያወሉ ቆይታቸው መልካም እንዲሆን የተቻለውን እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስታዳራቸው 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ከ200 በላይ የሚሆኑ ኩባኒያዎች በስራ ላይ የሚሚገኙ ሲሆን ኩባኒያዎቹ ከ100 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ስራ እድል መፍጠር ችለዋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#weekend
#specialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30