የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኤፍዲአይ ኢንተሊጀንስ አመታዊ ውድድር ሁለተኛ ወጣ
የኤፍዲአይ ኢንተሊጀንስ መጽሄት በሚያካሄደው አመታዊ ውድድር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሁለተኛ መውጣቱን አስታወቀ፡፡
የእንግሊዙ ፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ አካል የሆነው የኤፍዲአይ ኢንተሊጀንስ መጽሄት በየአመቱ በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በአህጉር ደረጃ እያወዳደረ ዝርዝር የሚያወጣ ሲሆን በዚህ አመት ዝርዝሩ ውስጥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአፍሪካ ካሉ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አስተዳዳሪዎች ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሽ ዝርዝር ውስጥ አካቶታል፡፡
መጽሄቱ በአፍሪካ ምርጥ ኢንዱስትሪ ዞን ዝርዝር ውስጥ የቤኒኑን ግሎ ጂግቤ ኢንዱስትሪ ዞን (Glo-Djigbé Industrial Zone) አንደኛ ሲሆን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል፡፡
እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2014 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መቋቋሙን ያተተው የመጽሔቱ ማብራሪያ ኮርፖሬሽኑ በስሩ 11 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን እና ሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚያስተዳድር አስታውሷል፡፡
ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ እና ፓርኮቹ በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ አተኩረው መስራታቸውንም በማብራሪያው ተመልክቷል፡፡ ይህም በዓለም ዙሪያ ስመጥር የሆኑ እንደ ደቡብ ኮርያው የስፖርት ትጥቅ አምራቹ ሽንትስ እና እንደ ጃፓኑ ቶዮ ሶላር ያሉ ኩባኒያዎች የማምራቻ ፋብሪካዎቻቸውን ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድረቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ እንዲመሰርቱ ማስቻላቸውን መጽሄቱ ባወጣው ማብራሪያ አመላክቷል፡፡
የመጽሄቱ የዳኖች ቡድን በዚህ የፈረንጆችን አመት ዝርዝር ውስጥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸውን ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን እና ፓርኮች ገምግመው ውጤት ለመስጠት ኮርፖሬሽኑ ወደሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ባለሀብቶችን ለመሳብ የሚከተለው ዘርፍ ተኮር የማስተዋወቅ ዘዴ፣ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ዘርፍ ተኮር መሆናቸው፣ ለባለሀብቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር መደራጀታቸው እና ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ጋሬጣ በመፍጠር ላይ የሚገኘውን የታሪፍ እርምጃ ኮርፖሬሽኑ የውሰደውን መፍትሄ እንደ መመዘኛ መውሰዱን ጠቁሟል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#KombolchaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#hawasaspecialeconomiczone
#fdiintelligence
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30