ልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ በጥራት ስራ አመራር ስርዓት ዘርፍ (QMS) እውቅና ተሰጠው
ሃዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በጥራት ስራ አመራር ስርዓት ዘርፍ (quality management system ISO 9001-2015) ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
በእውቅና አሰጣጥ ስነ _ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም ከተማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በጥራት ስራ አመራር እውቅና ማግኘቱ ትልቅ ስኬት መሆኑንና በዞኑ የሚገኙ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተቀባይነት እንዲኖራቸዉ ያስችላል ብለዋል፡፡
የሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አሸናፊ በበኩላቸው ዞኑ በጥራት ስራ አመራር ዘርፍ ያገኘው እውቅና በሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ደረጃ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቆሻሻ አወጋገድ ረገድ ላሳየው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ISO/14001:2015 (EMS) ፤ በላብራቶሪ አስተዳደር ስርዓት ISO/IEC17025:2017 የአለም አቀፍ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት እና ከኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ማግኘቱን አስታውሰው በቀጣይም በኢነርጂ ኦዲት እውቅና ለማግኘት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክብረአብ አበራ የተሰጠው እውቅና በዓለም አቀፍ የስራ አመራር ስርዓቶች መሰረት ለሚሰጡት አገልግሎት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለእውቅና አሰጣጥ ስነ_ስርዓቱ መሳካትአስተዋጻኦ ላበረከቱ እና በበላይነት ስራውን ላስተባበሩ ባለሙያዎች ፤ተቋማት እንዲሁም ማህበራት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#KombolchaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#hawasaspecialeconomiczone
#GIZ
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30