ከጀርመን እና ከእንግሊዝ ኤምባሲዎች የተውጣጡ ከፍተኛ ልኡካን ቡድን አባላት ሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን ጎበኙ
በኢትዮጵያ የጀርመን እና የእንግሊዝ ኤምባሲ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን አባላት በሀዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በጀርመን ተራድኦ ድርጅት (GIZ) እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የጀርመን ተጠባባቂ አምባሳደር ፈርዲናንድ ቮን ዌይ (ዶ/ር) በእንግሊዝ ኤምባሲ የልማት ዳይሬክተር አማንዳ ማክሎውሊን፤ እና በዩኬ ኤምባሲ ምክትል የልማት ዳይሬክተር ራቻኤል ፍላኸርቲ የተመራው የልዑካን ቡድኑ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በልማት ድርጅቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ከመጎብኘታቸው በተጨማሪ ውይይቶችን አካሂደዋል።
ልዑካኑ በጉብኝታቸው ወቅት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም ከተማ እና የሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማቲዎስ አሸናፊን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ አባላት ከሀዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባለሃብቶች ማህበር አባላት ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ያሉ ባለሃብቶችን የስራ እንቅስቃሤን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የጀርመን ተራዕዶ ድርጅት ዘላቂ የኢንደስትሪ ክላሰተር ሁለት በተባለው ፐሮጀክቱ በኩል ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ድጋፍ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡ ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት አምራቾች በአውሮፓ ገበያ ማፈላለግን ጨምሮ የሰራተኞችን የስራ ከባቢ ለማሻሻል እና አካባቢ ጥበቃ ላይ በማተኮር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ዘላቂ የኢንደስትሪ ክላሰተር ፐሮጀክት ሁለት በእንግሊዝ እና በጀርመን መንግስታት ድጋፍ እየተካሄደ ያለ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#KombolchaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#hawasaspecialeconomiczone
#GIZ
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30