በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከ680ሺ በላይ የስራ እድል በዚህ አመት መፈጠሩን የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ለምክር ቤት አባላት ኢንዱስትሪን በተመለከተ ባቀረቡት ማብራሪያ ላይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከ680ሺ በላይ የስራ እድል በዚህ አመት መፈጠሩን ገለጸዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ዘርፍ 12 በመቶ ገደማ ዕድገት ለማምጣት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒትሩ ጠቁመው ኢትዮጵያ ታምርት በሚል ንቅናቄ ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውንም አመላክተዋል፡፡ በዚህ ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ59 በመቶ ወደ 65 በመቶ ማደጉንም አንስተዋል።
የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የኃይል ፍላጎት 40 በመቶ እድገት ማሳየቱን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒትሩ ለእድገቱ የሲሚንቶ የብረት ውጤቶች እና የመስታወት ፋብርካ ለፍላጎቱ ማደግ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቁመዋል፡፡
በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች በበጀት ዓመቱ ለ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ ጠቁመው በግብርና ዘርፍ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ፣ በኢንዱስትሪ 680 ሺህ ገደማ፤ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ግማሽ ሚሊዮን ገደማ ዜጎች፣ በርቀት ስራ 60 ሺህ ገደማ እና በአገልገሎት ዘርፍ ቀሪው የስራ ዕድል ለዜጎች መፈጠሩን አውስተው አሁንም ሰፊ ስራ ዕድል ለዜጎች መፍጠር እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል፡፡
በዚህ ዓመት ከወጪ ንግድ 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን የጠቆሙት ይህም ከታቀደው 3 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ከሬሚታንስ 7 ቢሊዮን ዶላር፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 4 ቢሊዮን ዶላር፣ ከአገልግሎት 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱንም አመላክተዋል። አምና የውጭ ምንዛሬ ማግኛ መንገዶችን ከብድርና እርዳታ ውጭ ያሉትን ተጠቅመን ያገኘነው 24 ቢሊዮን ዶላር ነበር፤ ዘንድሮ 32 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስታዳድራቸው 10 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች፣ 2ፓርኮች እና ድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ለ100 ሺህ ገደማ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡
#PMO
#InvestInEthiopia
#IPDC
#HPR
#EthiopiaRising
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#constructionbusiness
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30