በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ወደብ ለማድረስ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ወደ ጅቡቲ ወደብ ለማድረስ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ አምራቾች በሎጅስቲክ ዘርፍ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍና በኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።
በውይይት መድረኩ የተገኙት የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚመረቱ ምርቶችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት እንዲሁም በተለያዩ አማራጮች ጭምር ወደ ጁቢቲ ወደብ ለማቅረብ የሚያስችል የተሻለ አማራጭ ማቅረባቸውን ገልፀው ለዚህም ውጤታማነት አስፈላጊ የሆነ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ ካሚል ኢብራሂም በበኩላቸው በአክሲዮን ማህበሩ በኩል የቀረበው የሎጅስቲክስ አማራጭ የአምራቾችን ችግር የሚቀርፍና በዘርፉ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚጨምር መሆኑን ገልፀው ለስኬታማነቱም በቅርበት እንሰራለን ብለዋል።
በቀጣይም ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የአክሲዮን ማህበሩን ቋሚ ቢሮዎችን በመክፈት አገልግሎቱን በቅርበት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ በመድረኩ ተገልጿል።
#IPDC
#KilintoSEZ
#NewBeginnings
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#InvestInEthiopia
#SEZ
#BusinessGrowth
#jobcreation
#railway
#EDR
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30