• Striving for eco industrial park
logo

ለወጣት ዲፕሎማቶች በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንቨስትመንት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ለወጣት ዲፕሎማቶች በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንቨስትመንት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር  ለወጣት ዲፕሎማቶች ባዘጋጀው ስልጠና ላይ በኢንቨስትመንትና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናውን የሠጡት  የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ  ዘመን ጁነዲን የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮች ከልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች   ጋር አያይዘው ያብራሩ  ሲሆን በተለይም በመንግስት የተተገበረው ሀገር  በቀል  የኢኮኖሚ ሪፎርም ፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ አቅራቢያ ያላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንደሚያደርጋት ገልጸዋል፡፡

አቶ ዘመን  በተጨማሪም  ወጣት ዲፕሎማቶቹ ኢትዮጵያን ቀዳሚ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን በንቃት እንዲያስተዋውቁ የጠየቁ ሲሆን  ጊዜው በኢንቨስትመንት እና በዲፕሎማሲ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ውጤታማ ለማድረግና ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት  ኮርፖሬሽኑ የበኩሉን ጥረት ያደርጋል ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፤ነጻ የንግድ ቀጠና እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ከተጠሪ ተቋማት፤ከዲፕሎማቶች፤ከኤምባሲዎችና ከኢንስቲትዩቶች ጋር በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

IPDC Enhances Awareness among Trainee Diplomats on Investment and Special Economic Zones

The Industrial Parks Development Corporation (IPDC) gave an awareness training session for young diplomats currently undergoing training at the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia, in collaboration with the ministry and Institute of Foreign Affairs.

During the session, Mr. Zemen Junedin, the Chief Investment Promotion and Marketing Officer of the corporation, presented key insights into Ethiopia's untapped investment potential, with a specific focus on Special Economic Zones. He discussed the outcomes of the country’s homegrown economic reforms and highlighted Ethiopia’s strategic location near the Red Sea and the Indian Ocean as an advantage for investment.

Mr. Zemen encouraged the trainees to actively promote Ethiopia as a prime destination for Foreign Direct Investment (FDI). The session is part of IPDC’s broader initiative to strengthen the relationship between investment and diplomacy, ensuring that Ethiopia’s investment opportunities are effectively communicated and maximized for the country’s sustainable development.

#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark 
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone 
#InvestInEthiopia  
#BahirDarSEZ  
#BusinessGrowth  
#JobCreation
#foreigninstitute
#mofa 
#investinethiopia 
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30