ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
በጅማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ 5 የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ገብተው ለማልማት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ጅማና አካባቢዋ ያላቸውን የተፈጥሮ ጸጋ በፋብሪካ በማቀነባበር ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር ለሚያደርጉት ጥረት ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ፍሰሃ በተጨማሪም የስምምነት ፊርማው የጅማንና የአካባቢውን ጸጋ ወደ ዘላቂ ሀብት ለመቀየር በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት ውስጥ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወትና የከተማዋን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ኩባንያዎቹ ሼድና የለማ መሬት የተረከቡ ሲሆን ወደ ስራ ሲገቡም ቡና በማቀነባበር እና የእንጨት ውጤቶች በማምረት ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ከ1200 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ዜጎችም የስራ እድልን ይፈጥራሉ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አልምቶ ከሚያስተዳድራቸው አስር ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ አንድ ነጻ ንግድ ቀጠና፣ ሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የጅማ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አንዱ ሲሆን ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በ150 ሄክታር ላይ ያረፈ 9 የማምረቻ ሼዶችን እና የለማ መሬት የያዘ ግዙፍ የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ ማዕከል ነው ፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#InvestInEthiopia
#BahirDarSEZ
#BusinessGrowth
#jobcreation
#agroprocessing
#jimmaspecialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30