• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 days, 8 hours ago
  • 26 Views

ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ጸጋ በጃፓን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል

ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ጸጋ በጃፓን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ መካሄድ ላይ ባለው በ33ኛዉ ኤዢያ፤ አረብ እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ጸጋ  በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የተመራ የኮርፖሬሽኑ አመራር ቡድን በኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና የነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ማበረታቻዎች ለፎረሙ ተሳታፊዎች እና ኢትዮጵያ ውስጥ መዋለ-ንዋይ ለማፍሰስ እውቀታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ፍላጎት ላሳዩ ባለሀብቶች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

 መንግስት የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለዉጭ ባለሀብቶች የበለጠ ቀልጣፋ፤ ሳቢ እና ተመራጭ ለማድረግ የወሰዳቸዉን የፖሊሲ ማበረታቻዎች፤ ሀገር በቀል የሪፎርም ስራዎችን እና በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ዉስጥ ያሉ የአንድ መስኮት አገልግሎቶችን በተመለክተ ዋና ስራ አስፈጻሚው ለታዳሚዎቹ በሰፊው አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰፊ ወጣት የሰው ሃይል ያላት ሀገር መሆኗ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ያደርጋታል ያሉት ዶ/ር ፍሰሃ አክለውም ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸዉ የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችና የነጻ ንግድ ቀጠና ዉስጥ ያሉ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም በቂ የኤሌክትሪክ ሃይል በተመጣጣኝ ዋጋ ለኢንቨስተሮች መቅረቡ፣ ምቹ መልካ ምድራዊ አቀማማጥ፣ በዙሪያዋ ሰፊ የገበያ እድል መኖሩ ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፍ ባለሃብቶች የበለጠ ተመራጭ መዳረሻ ያደርጋታል ብለዋል፡፡

በፎረሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በጃፓን የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ በበኩላቸዉ አሁን ላይ ኢትዮጵያ በበርካታ መመዘኛዎች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሀገር ሆናለች ያሉ ሲሆን መንግስት ከዚህ ቀደም የኢንቨስትመንት ዘርፉ ዋነኛ ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በመለየት የወሰዳቸዉ እርምጃዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች በአጭር ጊዜ ለዉጥ እያመጡ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

The Corporation Promotes Ethiopia's Special Economic Zones to Potential Investors in Tokyo

The Industrial Parks Development Corporation (IPDC) is promoting the investment opportunities available within Ethiopia’s Special Economic Zones (SEZs) to potential investors during the 33rd edition of the Asia, Arab, and Africa Investment Forum in Tokyo, Japan.

A high-level delegation from IPDC, led by CEO Dr. Fisseha Yitagesu, is showcasing the benefits and incentives that Ethiopia offers through its special economic zones and free trade zone to forum participants and foreign investors. 

According to the CEO, the delegation's main objective is to highlight Ethiopia's strategic position as a prime destination for investment.

Dr. Fisseha emphasized that the Ethiopian government has recently implemented a range of favorable investment policies designed to create an attractive and efficient investment climate. Key reforms include the introduction of the Homegrown Economic Reform, the adoption of a free-floating exchange regime, and the ratification of the Special Economic Zone Proclamation, which facilitates a one-stop-shop service within the special economic zones.

Additionally, Dr. Fisseha underscored Ethiopia’s youthful workforce and the corporation’s efforts to develop modern infrastructure within the special economic zones. He also pointed out the availability of reliable and competitively priced electric power as another key factor that makes the country particularly appealing to foreign investors.

In his opening remarks at the forum, Ethiopia’s Ambassador to Japan, Daba Debele, highlighted the wide array of investment opportunities across Ethiopia. He noted that the government's reforms, which aim to address past challenges in the investment sector, have already begun yielding positive results.

#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#japaninvestment  
#specialeconomiczone
#japan 
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30