• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 days, 9 hours ago
  • 32 Views

ሁዋጂያን ኩባንያ በድሬዳዋ  ነጻ የንግድ ቀጠና

የቻይናው  ሁዋጂያን ኩባንያ በድሬዳዋ  ነጻ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት ሊያደርግ ነው

በቻይና ሃገር የተለያዩ  ቆዳ ጫማዎችን በማምረት ታዋቂ የሆነው ሁዋጂያን ግሩፕ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ገብቶ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የሁዋጂያን ኢትዮጵያ  ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ሁአ ሮንግ ዣንግን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ዶ/ር ፍሰሃ በውይይቱ ሁዋጂያን ግሩፕ ባለፉት  ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማንቀሳቀስና ለወጣቶች የስራ እድልን በመፍጠር፤በእውቀትና ክህሎት ሽግግር አይነተኛ ሚናን እየተጫወተ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይም በንግድ ቀጠናው ለሚያከናውናቸው ስራዎች አስፈላጊውን እገዛ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ 

የሁዋጅያን ኢትዮጵያ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሚስተር ሁአ ሮንግ ዣንግ በኩላቸው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ውስጥ  ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን ላይም በድሬዳዋ ገብተው ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሁዋጅያን ኢትዮጵያ ኩባንያ እኤአ በ2015 ጀምሮ እየሰራ ያለ ኩባንያ ሲሆን አሁን ላይ ከ150 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት የሚያንቀሳቅስና ከ12000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ የስራ እድልን የፈጠረ ኩባንያ ነው፡፡

#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#eco industrial park
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone 
#Madeinethiopia
#specialeconomiczone

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30