• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo

የፉጃን ባለሃብቶችን ተሳትፎ

የፉጃን ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን  ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፦ፍሰሃ ይታገሱ

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የቻይናዋ ፉጃን ግዛት ባለሃብቶችን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል የሚደረግ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡  


ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት ከቻይና ፉጃን ግዛት የመጡ ከፍተኛ የመንግስት ልኡካን ቡድንን አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡


ዶ/ር ፍስሃ በውይይቱ ቻይናና ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ተሳትፎ በኩል ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ከፉጃን ግዛት ጋር የሚኖረው የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በማሳደግ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር ያግዛል ብለዋል፡፡


ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የፉጃን ግዛት ባለሃብቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማት የተሟላላቸው የማምረቻ ሼዶችንና የለማ መሬት ከተለያዩ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች ጋር መዘጋጀቱን ገልጸው ከግዛቲቱ በኢትዮጵያ ሀብታቸውን እና እውቀታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ለሚወስኑ ባለሀብቶች ስኬታማነት ኮርፖሬሽኑ ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


 የፉጃን ግዛት የፖለቲካ ቆንስላ ምክትል ሊቀመንበር እና የልዑካን ቡድኑ መሪ  ሁዋንግ ዌንሁይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ያለውን የዉጭ ባለሃብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ያከናወናቸው የማሻሻያ ስራዎች እና ኢንዱስትሪ ፓረኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን እንዲሸጋገሩ ማድረጉ የግዛቲቷ ባለሀብቶች  በግብርና ፤በቴክስታይል፤ በኤሌክትሪክ መኪና  መገጣጠም ዘርፍ እና በሌሎችም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ያካበቱት ልምድ ስራ ላይ እንዲያውሉ ያስችላል ብለዋል፡፡


የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የፉጃን ግዛት አስተዳደር በቀጣይም ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው የተጨማሪ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ግንባታና ማስፋፊያ ዕቅዶች ላይም በጋራ እንደሚሰሩ ተጠቁሟል ፡፡


#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#eco industrial park
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone 
#Madeinethiopia
#semeraspecialeconomiczone
#fuijan
#chinainvestment
#fujanspecialeconomiczone
#fuijanprovince

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30