• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 3 weeks ago
  • 455 Views

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ኩባንያ

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ኩባንያ ተመርቆ ስራ ጀመረ
 
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ7000ካሬ ሜትር  ላይ ያረፈውና ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የህፃናትና አዋቂ ጫማዎችን የሚያመርት ገሊላ ማኑፋክቸሪንግ የተባለ ኩባንያ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል። 

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የኮርፖሬት ሃብት ማኔጅመንት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ ኩባንያው በቆዳ ቴክኖሎጂ ሀገራችንን አንድ ደረጃ ከፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ አልፎ ለበርካታ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችም በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል፡፡ 

አቶ አለማየሁ በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸውና ግዙፉ በሆነው የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የፋብሪካውን ግንባታና ማሽነሪ ተከላ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ጨምረው ገልፀዋል።

ኩባንያው የተለያዩ አይነት ጫማዎችን የሚያመርቱ ሲሆን ምርቶቹንም ለሀገር ውስጥ ገበያ ከማቅረቡ በተጨማሪ ወደ ተለያዩ  የአውሮፓ ሃገራት እንደሚልኩ የኩባንያው ስራ አስኪያጅ እና ባለቤት በርሄ አሰፋ ገልፀዋል።

ኩባንያው አሁን ላይ በቀን 2000 ጥንድ ጫማዎችን የሚያመርት ሲሆን በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምርም 4000 ጫማዎችን እንደሚያመርትና ከ4000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል። 

ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው ግዙፍ 13 የኢንቨስትመንት ማዕከላት አንዱ ሲሆን በፓርኩ ውስጥ የተገነቡ 24 የማምረቻ ሼዶች በኮርያ፣ በቻይና ፣ በሕንድ፣ በጃፓን፣ ፈረንሳይ እና  በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የተያዙ ሲሆን ከከ26000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል። 


#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#eco industrial park
#Bolelemi
#industrypark
#investment
#leather


በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://lnkd.in/dJN-5uuY
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት https://t.me/ipdctchatbot