• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 weeks, 6 days ago
  • 136 Views

የፓኪስታን  ባለሀብቶች ኢንቨስትመንት

የፓኪስታን ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

የፓኪስታን  ባለሀብቶች ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና   በአልሙኒየም፣ ብረታ ብረትና የፓኬጂንግ ወረቀት ምርት ዘርፍ ላይ ገብተው  ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን የፓኪስታን ባለሃብቶችን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ 

ዋና ስራ አስኪያጁ በውይይቱ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ያሉ መሠረተ ልማቶችን፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን እና ጠቀሜታዎች ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

አቶ ሽፈራው  በሃገሪቱ ያለው ወጣትና የተማረ የሰው ሃይል ፤ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ  እንዲሁም በመንግስት በኩል የተሠጠው ከፍተኛ ትኩረት ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ኢንቨስት ለማድረግ  ትክክለኛ ቦታ መሆኑን ጭምር  አብራርተውላቸዋል፡፡

የፓኪስታን ባለሃብቶች በበኩላቸው በኢትዮጵያ በኩል ያለው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታና አማራጮች መኖራቸውን ገልጸው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በአልሙኒየም፤ብረታ ብረትና የወረቀት ፓኬጂንግ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ  የሚያስችላቸውን የቅድመ ኢንቨስመንት ጉብኝት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጠና የፓኪስታን ባለሃብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል፡፡

#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park 
#ForeignDirectInvestmentI
#Investment
#Pakistan