• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 months, 4 weeks ago
  • 614 Views

600 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር

#የምትተክል_ሃገር_የሚያጸና_ትውልድ !!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኩ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት፤የመምሪያ ኃላፊዎች፤የኢንዱስትሪ ፓርኩ አመራሮች፤ሰራተኞች፤ባለሀብቶች፤ የፀጥታ አካላት  እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ  ተሳትፈውበታል።

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተካሄደውና የዋና መስሪያ ቤት፤የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት እና የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማህበረሰብ በተሳተፈበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ91ሺ በላይ ችግኞች ተተክለዋል፡፡
 
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዓብይ አህመድ(ዶ.ር) የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጠና አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡