ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠናን ጎበኙ
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ተመስገን ጥሩነህ የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ጎብኝተዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ተመስገን ጥሩነህ ከድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር ፤ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሃ ይታገሱ(ዶ/ር) ፤ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች እና የፌዴራልና የድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመሆን በድሬዳዋ የንግድ ቀጠናን የአምራች ኩባንያዎችን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡