• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months, 1 week ago
  • 469 Views

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም ዋና ኢኮኖሚስት

"በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለአግሮ ፕሮሰሲንግ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል" - ዶ/ር ማክሲሞ ቶሬሮ 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለአግሮ ፕሮሰሲንግ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም ዋና ኢኮኖሚስት ዶ/ር ማክሲሞ ቶሬሮ ገልፀዋል። 

ዋና ኢኮኖሚስቱ ይህን የገለፁት በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ደሚቱ ሀምቢሳ እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ ጋር በመሆን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የምርት ሂደትን በተመለከቱበት ወቅት ነው። 

ዶ/ር ማክሲሞ በቆይታቸው በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙትን ሱፍሌ ማልት ኢትዮጵያ የቢራ ብቅል አምራች እና ሺንትስ የተሰኘ የጨርቃጨርቅ አምራች ኩባንያን የምርት ሂደትን ተዟዙረው ተመልክተዋል። 

በምልከታቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንና ይህም ለኢንቨስትመንት ፍሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አክለዋል። 

"Convenient conditions have been created for the agro-processing investment sector in industrial parks" - Dr. Maximo Torero 

Maximo Torrero, Chief Economist of the United Nations Food Program, stated that favorable conditions have been created for the agro-processing investment sector in industrial parks. 

The Chief Economist stated this when he observed the production process of Bole Lemi Industrial Park together with the Ethiopian Ambassador to Italy H.E Demitu Hambisa and the CEO of Industrial Parks Development Corporation, Dr. Fisseha Yitagesu. 

During his stay, Dr. Maximo toured and observed the production process of Souffle Malt Ethiopia, a beer malt manufacturer, and Shintz, a textile manufacturer located in the industrial park. 

He added that in his view, industrial parks have created a favorable environment for investors in various investment sectors, especially in the agro-processing sector, and this will greatly contribute to the flow of investment.