• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 months, 4 weeks ago
  • 398 Views

የኢትዮጵያና የኢራን ግንኙነትን በኢንቨስትመንት ማጠናከር

"የኢራን ባለሀብቶች በአግሮ ፕሮሰሲንግ እና መገጣጠም ዘርፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይሰራል" - አምባሳደር አሊ አክባር

የኢራን ባለሀብቶች በአግሮ ፕሮሰሲንግ እና በተሽከርካሪ መገጣጠም ዘርፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይሰራል ሲሉ በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር አሊ አከባር ገለፁ። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ አምባሳደሩን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አድርገዋል። 

በውይይታቸውም ሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት ያላቸውን የረጅም ጊዜ የጠበቀ ግንኙነት በኢንቨስትመንት ማጠናከር በሚቻልባቸውን ሁኔታዎች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ሁለቱም ሀገራት የብሪክስ አባል መሆናቸው ለኢንቨስትመንት ግንኙነቱ የጀርባ አጥንት እንደሚሆን አንስተው ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ ባለሀብቶች ብዝሀነት እንዲኖራቸው ለማድረግ በመላው አለም የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፍላጎቶችን አሟጦ ለመጠቀም እያደረገ በሚገኘው እንቅስቃሴ ኢራንም ተሳታፊ እንድትሆን ፍላጎት እንዳለ አረጋግጠዋል። በዚህም በቀጣይ የኢትዮ-ኢራን ኢንቨስትመንት ፎረምን ማዘጋጀት ጨምሮ ሌሎች አጋዥ ስራዎችን በጋራ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል። 

በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር አሊ አክባር በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባለፉት አመታት እየታየ ያለው እድገት በተለይም በኢነርጂ ዘርፍ የታየው ተስፋ ሰጪ ውጤት ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው የኢራን ባለሀብቶች በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ እና በተሽከርካሪ ማምረትና መገጣጠም  ዘርፍ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደሚሰራ አክለዋል። 

"Efforts will be made for Iranian investors to invest in industrial parks in agro-processing also vehicle manufacturing and assembly sectors" - Ambassador Ali 

Iran's ambassador to Ethiopia, Ali Akbar, said that efforts will be made for Iranian investors to invest in industrial parks in the fields of agro processing and vehicle manufacturing and assembly. 

Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu received the ambassador at his office and had a discussion. 

During the discussion, the two officials  exchanged ideas on ways to strengthen their long-term relationship through investment. 

IPDC CEO, Dr. Fisseha, pointed out that the BRICS membership of both countries will be the backbone of the investment relationship and confirmed that there is a desire for Iran to participate in the movement that IPDC is making to attract investment from all over the world to ensure that investors diversification in its investment centers. He additionally mentioned that other initial tasks should be done together, including the preparation of the Ethio-Iran Investment Forum. 

Ali Akbar, Iran's ambassador to Ethiopia, mentioned that the promising development results seen in Ethiopia over the past years, especially in the energy sector, is created  favorable conditions for investment, and added that he will work for Iranian investors to invest, especially in the agro-processing and vehicle manufacturing and assembly sectors.