ኮርፖሬሽኑ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ4.4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ጎፋ ዞን ፤ ገዜ ጎፋ ወረዳ ፤ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ4.4 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አድርጓል።
የገንዘብና የአይነት ድጋፋን ያስረከቡት የመሬትና መሰረተ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ፀጋየ ዘካርያስ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ማዘናቸውን ገልጸው ኮርፖሬሽኑ በቀጣይም ለተጎጅ ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ አደጋው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ መላዉ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ማስመስከራቸውን ገልጸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንም ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።