• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months, 2 weeks ago
  • 433 Views

ሱፍሌ ማልት ኢትዮጵያ

"ሱፍሌ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት እንዲያስፋፋ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን" - ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ሱፍሌ የብቅል አምራች ኩባንያ ያለውን ኢንቨስትመንት እንዲያስፋፋ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ገልፀዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት ከሱፍሌ ማልት ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ቶማስ ኔቪው ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። 

በውይይታቸውም ኩባንያው  ስላለበት ወቅታዊ የምርት ሂደት ፤ ተኪ ምርትን ስለማሳደግና ስለ ኤክስፖርት እንዲሁም ስለ ቀጣይ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ኩባንያው ኢትዮጵያ የቢራ ገብስ ብቅልን በአጭር ጊዜ ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ላደረገችው ጥረት ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱንና እንደ ኬንያ ላሉ ለምርቱ ከፍተኛ ፍላጎት ላላቸው ሀገራት ኤክስፖርት ማድረግ መጀመር እንደሚገባው ጠቁመው በቀጣይም በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በወሰደው ተጨማሪ የ2 ሄክታር መሬት ላይ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያውን እንዲጀምር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግለት አረጋግጠዋል። 

ሱፍሌ ማልት ኢትዮጵያ እውቅ የፈረንሳይ የቢራ ገብስ ብቅል አምራች ሲሆን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ፈሰስ በማድረግ ኢትዮጵያ ከውጪ ታስገባው የነበረውን የቢራ ገብስ ብቅል ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ በመተካት በኩል ትልቁን ድርሻ የሚወስድ ከ 110 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል አርሲና ባሌ ዞኖች ለሚገኙ ከ60 ሺ በላይ ለሚሆኑ የቢራ ገብስ አብቃይ ገበሬዎች ዘላቂ ገበያ የፈጠረ ኩባንያ ነው። 

ኩባንያው በ2016 በጀት ዓመት ብቻ ከ 5.6 ቢሊዮን ብር በላይ ተኪ ምርት ያመረተ መሆኑም ተመላክቷል። 

"We will provide all the necessary support for Souffle to expand its investment in Ethiopia" - Dr. Fisseha Yitagesu 

Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu said that IPDC will provide all the necessary support to expand the investment of Souffle Malt Manufacturing Company located in Bole Lemi Industrial Park. 

The CEO disclosed this in a discussion with Thomas Neveu, General Manager of Souffle Malt Ethiopia. 

In their discussion, they exchanged productive ideas about the company's current production process, increasing production and exports as well as further investment expansion. 

IPDC CEO, Dr. Fisseha, pointed out that the company has made a great contribution to Ethiopia's effort to completely replace beer barley malt with domestic production and that it should start exporting to countries like Kenya that have a high demand for the product. He additionally confirmed that the company will be given comprehensive support to start its investment expansion on the additional 2 hectares of land it took at Bole Lemi Industrial Park. 

Souffle Malt Ethiopia is a well-known French beer barley malt producer, and by investing huge capital in Bole Limi Industrial Park, it has created job opportunities for more than 110 citizens and market linkage for more than 60,000 farmers in Arsi and Bale zones in the Oromia region. 

It was also pointed out that the company produced more than 5.6 billion Birr import substituting product in 2016 fiscal year.

#Importsubstitution