በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለው የኢኮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እሳቤ አበረታች መሆኑ ተገለፀ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለው የኢኮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እሳቤ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል። በምልከታቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎችን በመጎብኘት ከሀገር በቀልና ከውጪ ኢንቨስተሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም አምራች ኩባንያዎች ስላሉበት የምርት እንቅስቃሴ ፤ የስራ እድል ፈጠራ ፤ የኤክስፖርት እና የተኪ ምርት ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ሀሳብ ተለዋውጠው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችና አፈፃፀሞች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለኢንቨስተሮች ያለው ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ እና በፓርኩ ለኢኮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት የተሰሩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እንደ ሀገር የሚከናወነውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በእጅጉ የሚያግዙ መሆናቸውም በእለቱ ተገልጿል።
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ከነበረው ፕሮግራም ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርም ተከናውኗል።
'The strive for Eco Industrial Park excellence in Kombolcha Industrial Park is encouraging' - Dr Fisseha Yitagesu
Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr Fisseha Yitagesu stated that the strive for Eco Industrial Park excellence in Kombolcha Industrial Park is encouraging.
The CEO observed Kombolcha Industrial Park's current operational activities. During his observation, he visited manufacturing companies producing in the industrial park and held discussions with local and foreign investors.
In their discussion Dr. Fisseha exchanged detailed ideas with the investors on issues such as job creation, export and import substitution, and set directions for issues and implementations that require prioritized attention.
It was also underlined that the industrial park's favorable environment for investors and the green development works done by the park for the development of eco industrial park will greatly help the country's green legacy program.
Along with the tour at the industrial park, a green legacy program was also carried out.