• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 6 months, 1 week ago
  • 705 Views

የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የኦፕሬሽን እንቅስቃሴ

"በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቅድመ ኦፕሬሽን ስራ እያከናወኑ የሚገኙ ኩባንያዎች ወደ ምርት ሂደት እንዲሸጋገሩ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል" - ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ ከአፋር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱ ሙሳ ጋር በመሆን የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው በፓርኩ የሚገኙ የቅድመ ኦፕሬሽን ስራ እያከናወኑ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች ያሉበትን ወቅታዊ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን በአፋጣኝ ወደ ምርት ሂደት የሚገቡበት አካሄድ ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለጅቡቲ ወደብ ያለው ቅርበት ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያደርገው መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ፍሰሀ በጋርመንትና ቴክስታይል ፤ በአውቶሞቢል መገጣጠም ፤ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር እና በሌሎችም የኢንቨስትመንት ዘርፎች ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። 

በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከነበረው ምልከታ ጎን ለጎብ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተከናውኗል። 

"The necessary support will be given to the companies that are doing pre-operational activities in Industrial Parks to start their production" - Dr. Fisseha Yitagesu 

Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu, together with the Mayor of Afar City Administration, Abdu Musa, observed the current operationql activities of  Semera Industrial Park. 

The CEO observed the current operational activities of the manufacturing companies in the park who are doing pre-operational work and set a direction for them to start the production process immediately. 

Dr. Fisseha called on investors to participate in investments in garments and textile, agro processing, car assembly and other sectors mentioning that the proximity of the industrial park to Djibouti Port makes it ideal for investment. 

In addition to the observation at Semera Industrial Park, a green legacy program was carried out at the Industrial Park.