• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 448 Views

ፕሮጀክት አገልግሎቱ ያጠናቀቀው

ፕሮጀክት አገልግሎቱ ለመሰቦ ስሚንቶ  ፋብሪካ የሰራውን ጥናት ሰነድ  አጠናቆ አስረከበ 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ የሰራውን የአዋጭነት ጥናት ሰነድ አጠናቆ በዛሬው እለት አስረክቧል። 

የጥናት ሰነዱን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ለመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ተወካይ አቶ ተከስተ ታደሰ አስረክበዋል። 

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ፕሮጀክት አገልግሎቱ ያለውን የረጅም ዓመት ልምድ ተጠቅሞ የትልልቅ ተቋማትን ስኬት ለማሳደግና አዳዲሶቹንም ውጤታማ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው አሁንም መሰቦ ስሚንቶን ወደ  ገናናነቱ ለመመለስ የሚያስችል የጥናት ሰነድ አጠናቀው ማስረከባቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተወካይ አቶ ተከስተ ታደሰ በበኩላቸው የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደተሻለ ስራ እንዲገባና ወደ ቀድሞ ክብሩ እንዲመለስ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሰራው የአዋጭነት ጥናት አጋዥ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ እንዲገባ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በሃገራችን የሚገኙ ትልልቅ ተቋማትን የአዋጭነት ጥናት በመስራት ወደ ትርፋማነት ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ያለ ተቋም ሲሆን ባለፉት ጊዜያት  የከሰም ፤ ጣና በለስና የፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎችን የጥናት ሰነድ አጠናቆ ያስረከበ መሆኑ ይታወሳል፡፡ 

Industrial Projects Service Completes Feasibility Study for Mesebo Cement Factory 

Industrial Parks Development Corporation’s Industrial Projects Service (IPS) has finalized and submitted a feasibility study for Mesebo Cement Factory. 

IPS General Manager Shiferaw Solomon formally handed over the document to Tekeste Tadesse, representative of Mesebo cement factroy. 

During the handover, IPS General Manager Mr. Shiferaw stated that IPS's extensive experience in large-scale projects is supporting huge institutions  to uplift their success and make new ones successful. He also expressed his confidence that the study will revitalize the Mesebo Cement Factory and restore its former prominence. 

Tekeste Tadese, the factory representative, stated that the feasibility study will be highly supportive in helping the factory regain its past production capacity. 

Imdustrial Projects Service (IPS) has a proven track record of conducting feasibility studies for large companies in the country, having previously completed studies for Kesem, Tana Beles, and Fincha Sugar Factories and others.