• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 452 Views

የኮርፖሬሽኑ የቀጣይ ሁለት አመታት ሮድ ማፕ

የኮርፖሬሽኑ የቀጣይ ሁለት ዓመታት ስትራቴጂክ ሮድ ማፕ ይፋ ሆነ 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚመራበትን ስትራቴጂክ ሮድ ማፕ ይፋ አድርገዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ሮድ ማፑን ይፋ ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ መድረክ ላይ ነው። 

"ፈጠራ እና ፍጥነት" በሚል ፅንሰሀሳብ ላይ ትኩረት ያደረጉት  ዋና ስራ አስፈፃሚው  ለለውጥ ዝግጁ እና ለተግባር ቁርጠኛ የሆነ አመራርና ፈፃሚ መፍጠር ላይ ጠንካራ ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል። 

ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ማዕከል የመቀየር ስራ ፤ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ፤ የሼድ የመያዝ ምጣኔን መቶ ፐርሰንት ማድረስ ፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ፤ የኢንቨስተሮችን እርካታ ማሳደግ በሮድ ማፑ አበይት ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አፅንኦት ሰጥተዋል። 

በሪሮርም እንዲተገበሩ እቅድ የተያዘላቸው ክንውኖች መኖራቸውንም ያሳወቁት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሪፎርሙ የመፍታት ምዕራፍ ፤ የመቀየር ምዕራፍ እና የማፅናት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቁመው በስትራቴጂ የተከፋፈሉ የሪፎርም ትግበራ ምዕራፎች እንደሚኖሩት በምዕራፎቹም መጀመር ፤ መጨመር ፤ መጨረስ እና መተሳሰር የተሰኙ ውቅሮች እንደሚኖሩት ተመላክቷል። 

ዶ/ር ፍሰሀ በመጀመር ፤ መጨመር እና መጨረስ እሳቤ ውስጥ አዳዲስ ሀሳቦችና ፕሮጀክቶችን ማሰብ ፤ ስራና ክንውኖችን መጀመር እና መጨረስ እንዲሁም ሌሎች  የተጀመሩ ተቋማዊ ግብን ለማሳካት የሚረዱ ስራዎችን ማጠናቀቅና ማስተሳሰርን እንደ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

ላለፉት ሶስት ቀናት በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል።