በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል መሳብ ተችሏል
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስትመንቶችን መሳቡ ተገልጿል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በማስቻልና ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት እንዲፈፅሙ መደረጉም በመድረኩ ተገልጿል።
ለኢንቨስትመንት ስበቱ ውጤታማነት አለም አቀፍና የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ ስራዎች ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተከናወኑ የቅንጅት ስራዎች እንዲሁም ሀገር ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ድርሻ እንዳላቸው በመድረኩ ተመላክቷል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት የፈረሙ አለም አቀፍና ሀገር በቀል ኩባንያዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ኦፕሬሽን ደረጃዎች ላይ እንደሚገኙ ሲገለፅ የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ፤ በማሽን ተከላና ሰራተኛ በማሰልጠን ላይ የሚገኙ እንዲሁም የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን አጠናቀው ወደ ምርት ሂደት የገቡ መሆናቸው ተመላክቷል።
More than 500 million dollars of investment capital was attracted in tha past fiscal year
It is stated that Industrial Parks Development Corporation attracted more than 500 million dollars in capital investments in the last fiscal year.
In the last fiscal year, local and international investors were allowed to invest and they were made to enter contractual agreement with the corporation.
Additionally International and local investment promotion activities, coordination activities carried out with the stakeholders as well as the country's economic reforms have a postive role for the effectiveness of the investment attraction.
International and local companies that have signed contracts with the corporation in the last fiscal year are in the process of pre-operation, machine installation, staff training and some have completed the pre-operational work and started the production process.