• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 436 Views

ከ237 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶች

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ237 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተኪ ምርት ለሃገር ውስጥ ገበያ ቀርቧል 

በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከ237 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተኪ ምርት ለሃገር ውስጥ ገበያ መቅረቡ ተገለፀ። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን በሃዋሳ ከተማ በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡ 

በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ237 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ማምረት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን በዚህም ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ከ606 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት እንደተቻለ በሪፖርት ተገልጿል፡፡ 

በ2016 በጀት ዓመት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱት ተኪ ምርቶች ውስጥ የቢራ ገብስ ብቅልና የኮንስትራክሽን እቃዎች ግብዓት ዋነኞቹ በተለይ የቢራ ፋብሪካዎች በግብዓትነት የሚጠቀሙትን የቢራ ገብስ ብቅል ሙሉ ለሙሉ መተካት መቻሉን በእቅድ አፈጻጸሙ ግምገማ ወቅት ተመላክቷል፡፡ 

በሌላ በኩል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ምርቶችን ለሃገር ውስጥ አምራቾች ለማቅረብ ከ124 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብዓቶችን ለአምራቾች በማቅረብ የገበያ ትስስር መፈጠሩንም በእቅድ አፈጻጸም ግምገማው ተጠቅሷል፡፡ 

237 + million USD of import substituting products were offered to the domestic market 

In 2016 fiscal year, more than 237 million USD of import substituting products were offered to the domestic market. 

Industrial Parks Development Corporation is currently evaluating the performance of the 2016 fiscal year in Hawassa City. 

It was stated that in the last fiscal year, import substituting products worth more than 237 million US dollars were produced in industrial parks, and since the establishment of the corporation, it has been possible to produce import substituting products worth more than 606 million US dollars, according to todays report. 

In the 2016 fiscal year, among the import substituting products produced by the industrial parks, it was pointed out that barley malt for breweries and construction materials took the highest share. 

On the other hand, it was also mentioned in the performance review that in the last fiscal year, market linkages were created by providing inputs worth more than 124 million US dollars to manufacturers in industrial parks.